በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕን የወንጀል ክስ ጉዳይ የሚዳኙት ከሕዝብ የተውጣጡ ዳኞች በሚሰጡት ብይን ዙሪያ እየተነጋገሩ ናቸው።
ትራምፕ፣ በ2016ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ላይ ተጽእኖ ለማሳደር በማሰብ፣ ለአንዲት የወሲብ ተዋናይት አፍ ማዘጊያ የፈጸሙትን ክፍያ በመሸሸግ የማጭበርበር ወንጀል ፈጽመዋል፤ በሚል ነው የተከሰሱት።
የዘንድሮው የምርጫ ዘመቻዎችም ከኒውዮርኩ ፍርድ ቤት ውጭ ቢቀጥሉም፣ የክሱ ሒደት ግርዶሽ የኾነባቸው ይመስላል፡፡
የአሜሪካ ድምፁ ዘጋቢ ስካት ስተርንስ ያጠናቀረውን ዘገባ አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።