በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል በ2016 በጀት ዓመት ዝቅተኛ የግብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ


በዐማራ ክልል በ2016 በጀት ዓመት ዝቅተኛ የግብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00

በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ በዐሥር ወራት ውስጥ የተሰበሰበው የግብር ገቢ፣ በበጀት ዓመቱ ከታቀደው ከግማሽ በታች እንደኾነ፣ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።

በበጀት ዓመቱ ከ71 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ቢታቀድም፣ ለመሰብሰብ የተቻለው 33 ቢሊዮን ብር ያህል እንደኾነ፣ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረ ማርያም ደጀኔ፣ ትላንት ሰኞ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዕቅዱ “እጅግ የተለጠጠ ነበር” ያሉት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፣ በተለይም በክልሉ ምዕራባዊ ዞኖች ያለው የጸጥታ ችግር ለግብር አሰባሰቡ ዕንቅፋት እንደፈጠረ ገልጸዋል፤ እስከ አሁንም 100ሺሕ የሚኾን ግብር ከፋይ ክፍያውን እንዳልፈጸመ አመልክተዋል።

በክልሉ አሁን አንጻራዊ ሰላም መኖሩን የገለጹት ምክትል ኃላፊው፣ በቀሪ ጊዜያት ነጋዴው ግብሩን እንዲከፍል ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ አንዳንድ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው፣ ግብር ዜግነታዊ ግዴታ እንደኾነ አምነው መክፈላቸውን ገልጸው፣ ለአርሶ አደሩ ግን የጤና መድኅን ከግብር ጋራ አብሮ እንዲከፍል መደረጉ አግባብ አለመኾኑን ተችተዋል።

XS
SM
MD
LG