በቀይ ባሕር የንግድ መሥመር ላይ ያጋጠመው አለመረጋጋት፣ ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ገበያ የምትልከው የቡና መጠን እንዲቀንስ ማድረጉን፣ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የመሥሪያ ቤቱ ዋና ዲሬክተር ዶር. አዱኛ ደበላ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ በቀይ ባሕር ዓለም አቀፍ የንግድ መሥመር ላይ የተከሠተው ቀውስ፣ አገሪቱ ወደ አውሮፓ ገበያ በምትልከው የቡና መጠን ላይ ተጽእኖ መፍጠሩን አውስተዋል። ለአብነትም ወደ ጀርመን ሲላክ የነበረው የቡና መጠን በግማሽ መቀነሱን ጠቅሰዋል፡፡