የእስራኤል ጦር ሠራዊት በጋዛ ሰርጥ እና በግብፅ መካከል የሚገኘውን፣ በጋዛ በኩል ያለውን የራፋ መተላለፊያ ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ ከግብጽ ጋራ በተደረገው ስምምነት ለመጀመሪያ ጊዜ ከደቡብ እስራኤል የርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ መኪኖች ወደ ጋዛ መግባት ጀምረዋል።
ግብፅ ጋዛ በፍልስጤማውያን ቁጥጥር እስኪኾን ድረስ የሚል ቅድመ ሁኔታን በማስቀመጥ፣ የፋራህን መሻገሪያ ለመክፈት ፈቃደኛ ሳትኾን ቆይታለች።
ነገር ግን በአሜሪካ እና በእስራኤል ግፊት፣ የትራፊክ ፍሰቱን ከራፋ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ በሚገኘው ኬረም ሻሎም ማቋረጫ በኩል ወደ ጋዛ ዋናው የካርጎ ጣቢያ ለማድረግ ተስማምታለች።
እስራኤል በራፋ ላይ ካደረሰችው ጥቃት በኋላ መሸጋገሪያው የማይደረስበት ኾኖ ቆይቷል።
እስራኤል በመቶዎች የሚቆጠሩ የጭነት መኪናዎች እንዲገቡ መፍቀዷን ብታስታውቅም፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ግን ርዳትን በዛ በኩል ማሳለፍ በጣም አደገኛ መኾኑን ገልፀው እያስጠነቀቁ ነው።
መድረክ / ፎረም