በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሃላ ሰየምት ወረዳ ከረኀብ ጉዳት ጋራ በተያያዘ አንድ ሰው መሞቱ ተገለጸ


በሰሃላ ሰየምት ወረዳ ከረኀብ ጉዳት ጋራ በተያያዘ አንድ ሰው መሞቱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:59 0:00

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሰሃላ ሰየምት ወረዳ፣ ባለፈው የመኸር ምርት ዘመን የተከሠተው ድርቅ ባስከተለው ረኀብ ምክንያት የተጎዱ ሰዎች ለኅልፈት መዳረጋቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ በወረዳው ያጋጠመውን ድርቅ ተከትሎ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ24ሺሕ በላይ ሰዎች መኖራቸውን ገልጸዋል፤ ባለፈው ሚያዝያ ወር፣ ከረኀብ ጉዳት የተነሣ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን፣ ከጤና ተቋማት ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል፡፡

በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የቢላዛ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማለደ ብሬ በበኩላቸው፣ በቢላዛ ቀበሌ ብቻ ባለፈው ወር ሁለት ሰዎች ከረኀብ ጉዳት ምክንያት መሞታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የርዳታ መቆራረጥ፣ የጸጥታ እና የመንገድ አለመኖር ችግሩን እንዳባባሰውም አስተዳዳሪው አክለዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል፣ ዛሬ ኀሙስ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ ከረኀብ ጋራ በተያያዘ የሰዎች ሕይወት ስለማለፉ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው፣ ነገር ግን “አጣራለኹ” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG