በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በላሊበላ ከተማ አቅራቢያ የቀጠለው ግጭት ለቅርሶች ደኅንነት ስጋት ፈጥሯል


በላሊበላ ከተማ አቅራቢያ የቀጠለው ግጭት ለቅርሶች ደኅንነት ስጋት ፈጥሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

ትላንት ማክሰኞ፣ በመከላከያ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ በዓለም ቅርስ መገኛዋ ላሊበላ ከተማ አካባቢ፣ በከባድ መሣሪያ የታገዘ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ መዋሉን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ፡፡

በተኩስ ልውውጡ ያልታጠቁ ሰዎች መጎዳታቸውን የተናገሩት የከተማዋ አስተያየት ሰጭዎች፣ በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚካሔደው የተኩስ ልውውጥ፣ በጉዳት ላይ በሚገኙት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንም ኾነ በዙሪያው ባሉት ታሪካዊ ቅርሶች ላይ የደኅንነት ስጋት ፈጥሯል፤ ይላሉ።

የዐማራ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አበበ እምቢአለ፣ የትላንቱን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ ያጋጠመ ጉዳት ስለመኖሩ የሚያውቁት እንደሌለ ገልጸው፣ በክልሉ የተቀሰቀሰው የጸጥታ ችግር የቱሪዝም እንቅስቃሴውን እንዳወከው ተናግረዋል፡፡

በትጥቃዊ ግጭት ውስጥ ለገቡ አካላትም ባስተላለፉት መልእክት፥ ግጭትን ከታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ቅርሶች አካባቢ በማራቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG