በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያን ሴቶች እየተገዳደረ ያለው የመሥመር-ላይ-ቴክኖሎጂ ጾታዊ ጥቃት እየጨመረ ነው


የኢትዮጵያን ሴቶች እየተገዳደረ ያለው የመሥመር-ላይ-ቴክኖሎጂ ጾታዊ ጥቃት እየጨመረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:24 0:00

ሴቶች በኢትዮጵያ፣ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ በመሥመር-ላይ-ቴክኖሎጂ የተደገፈ ጾታዊ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች፣ በማኅበራዊ ትስስር አማራጭ ቴክኖሎጂዎች አማካይነት፣ ጾታን መሠረት ያደረጉ አድልዎ እና ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው እንደሚገኙና በዚህም ምክንያት ዝም እንዲሰኙ፣ እንዲያፍሩና እንዲፈሩ መደረጋቸውን፣ ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን የተሰኘ ተቋም ያካሔደው አንድ ጥናት አመልክቷል።

እንደተቋሙ ጥናት፣ በጥቃቱ ምክንያት ሴቶች ኢንተርኔትን መጠቀም እስከማቆምና ማኅበራዊ መስተጋብራቸውን እስከመገደብ ደርሰዋል።

በኢንተርኔት ላይ የሚፈጸመውን ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት እና በሴቶች ላይ እያደረሰ ያለውን የሥና ልቡና ቀውስ አስመልክቶ፣ ስመኝሽ የቆየ፥ የጥቃቱን ተጎጂዎች እና የጥናቱን ተሳታፊዎች አነጋግራለች፤ ቀጥሎ ይቀርባል።

XS
SM
MD
LG