በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍርድ ቤት በእነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ዋስትና ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሳምንት ቀጠረ


ፍርድ ቤት በእነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ዋስትና ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሳምንት ቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:54 0:00

ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር በመሞከር ክስ የተመሠረተባቸው እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን፣ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤት የሳምንት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የእነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ጠበቆች እና ዐቃቤ ሕግ፣ ዛሬ ሰኞ፣ በዋስትና ጥያቄ ላይ ክርክር አድርገዋል፡፡ በዛሬው የችሎት ውሎ ክሱ በንባብ ከቀረበ በኋላ፣ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ እና ሁለተኛ ተከሳሽ የክስ መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ ችሎቱ፣ ለክስ መቃወሚያው የዐቃቤ ሕግን ምላሽ ለመጠባበቅና በዋስትናው ክርክርም ላይ ለመወሰን ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ከቀሲስ በላይ ጠበቆች አንዱን፣ ገብሩ ማኅተምን አስተያየት ያካተተውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG