ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሌተና ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ትላንት እሑድ ለክልሉ ብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የፌደራል የጸጥታ አካላት፣ ከራያ አካባቢ ውጭ በሌሎች አከባቢዎች “ሕገ ወጥ” ያሏቸውን አስተዳደሮች ማፍረስ እና ከመከላከያ ሠራዊት ውጭ ያሉ ኀይሎች ማስወጣት አለመጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህም፣ “የተፈናቃዮች አመላለስ ሒደቱን እያዘገየው ነው፤” ያሉት ሌተና ጄነራሉ፣ የፌደራል የጸጥታ ኀይሎች ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከፌደራል መንግሥት እና ከአማራ ክልል አመራሮች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡
በሌላ በኩል፣ በክልሉ ውስጥ የኮንትሮባንድ ንግድ እንዲሁም ሕገ ወጥ የሰዎች እና የመሣሪያ ዝውውር እየታዩ እንደሚገኙ በመግለጫቸው ላይ ያነሡት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ መፍትሔ በማበጀት የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት ይሠራል፤ ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያያዘው ፋይል ይከታተሉ።