በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ16 ዓመቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የፒኤችዲ ተማሪ ፀረ ቲቢ እንቅስቃሴ


የ16 ዓመቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የፒኤችዲ ተማሪ ፀረ ቲቢ እንቅስቃሴ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:46 0:00

ባለፈው የካቲት ወር፣ የ16ኛ ዓመት ልደቷን ያከበረችው ሐና ቴይለር ሽሊትዝ፣ በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኖርዝ ቴክሳስ የፒኤችዲ ትምህርቷን እንድትማር ጥሪ ሲቀርብላት፣ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከተቀበለችበት ከቴክሳስ ዎማንስ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪዋን የመቀጠል ዕድል አግኝታለች።

ከአርባ ምንጭ የተገኘችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሐና ቴይለር ሽሊትዝ፣ ወላጅ እናቷን በቲቢ በሽታ ምክንያት ዐጥታለች፡፡ የአንድ ዓመት ሕፃን ሳለች፣ ከአርባ ምንጭ የሕፃናት ማሳደጊያ በሕጋዊ ጉዲፈቻ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ስትመጣ፣ ራሷም በቲቢ በሽታ ተጠቅታ ክብደቷም 4ነጥብ5 ኪሎ ግራም ብቻ እንደነበረ ወላጆቿ ይናገራሉ።

አሁን ገና በአዳጊነት ዕድሜዋ የከፍተኛ ትምህርት አክሊልን የተቀዳጀችው ሐና፣ ከትምህርቷ ጎን ለጎን ቲቢን ከዓለም ላይ ለማጥፋት ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋራ እየሠራች ትገኛለች።

XS
SM
MD
LG