በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ዳግም በተነሣ ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ


በደቡብ ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ዳግም በተነሣ ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ እና ገላና ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በታጠቁ ሰዎች መካከል ውጊያ እየተካሔደ መኾኑን ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

በምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ አስተዳደር ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ጂኦ፣ ግጭቱ ትላንት ማክሰኞ መቀስቀሱንና አንድ አርብቶ አደር ሲገደል ሌላ አንድ መቁሰሉን፣ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ አረጋግጠዋል፡፡

የኮሬ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ በበኩላቸው፣ ከጃሎ እና ከሻፉለ ቀበሌዎች፣ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሰው መቀሰሉን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG