በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ብትቃውምም እስራኤል ጋዛ ላይ ጥቃት ፈጽማለች


ጋዛ ግንቦት 03/2016
ጋዛ ግንቦት 03/2016

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተጨናነቀችው ራፋህ ከተማ ላይ እስራኤል ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት ከፈጸመች ‘ከፍተኛ’ የሆነ ጥፋት እንደሚከተል ካስጠነቀቀ እና ዩናይትድ ስቴትስም የጦር ጥቃት ተቃውሞዋን በድጋሚ እንደ አዲስ ከገለጸችም በኋላ፤ እስራኤል ጋዛን ደብድባለች።

የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ጋዜጠኞች እስራኤል የባህር ጠረፍ አካባቢዎችን በማጥቃት የመንግስታቱ ድርጅት የረድኤት ሰራተኞች እንዳያልፉ መንገድ መዝጋቷን እና ይኸም የእስራኤል ወታደሮች አለማቀፉን ማስጠንቀቂያ ጥሰው ራፋህ ከመግባታቸው ጋር ተደምሮ በሁለቱም መንገዶች በኩል መፈናፈኛ እንዳሳጣቸው ዘግብዋል።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አርብ ዕለት ባወጣው ሪፖርት ምንም እንኳን እስራኤል የዋና ወታደራዊ አቅራቢዋ ዩናይትድ ስቴትስ የጦር መሣሪያ አጠቃቀምን እና ዓለም አቀፍ ህጎችን የጣሰች ቢሆንም ነገር ግን የጦር መሳሪያዎቹን ወደ እስራኤል ከመጫን ለማገድ የሚያደርስ በቂ ማስረጃ ዩናይትድ ስቴትስ አላገኘችም ሲል አስታውቋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርቱን ያቀረበው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ተጠልለዋል ብሎ ባስታወቀበት በራፋህ ከተማ ላይ እስራኤል የምታደርገውን ሁለንተናዊ

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG