በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ተጀመረ


የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:27 0:00

የቻይና የመሠረተ ልማት ግንባታ ፖሊሲ አካል የኾነው፣ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ፕሮጀክት፣ ዛሬ ሥራውን በይፋ ጀምሯል።

ቻይና፣ ሦስት አህጉራትን በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር የወጠነችው “የመቀነት እና መንገድ ማገናኛ ተነሣሽነት” (Belt and Road Initiative) አካል እንደኾነ የተገለጸው ፕሮጀክቱ፣ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሞጆ እና አዳማ ከተሞች መካከል እንደሚገነባ፣ የቻይና ባቡር ግንባታ ኃላፊ ዴይ ሄገን ገልጸዋል፡፡ “በዐይነቱ በቻይና-አፍሪካ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሳሌ የሚኾን ነው፤” ብለዋል።

በገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ኢትዮጵያ የነጻ ኢንዱስትሪ ቀጣናን ለማዘጋጀት፣ የፖሊስ ማሻሻያ ማድረጓን ገልጸዋል።

የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ያናገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሞያ ደግሞ፣ በቻይና ብድሮች የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች እና ሌሎችም ሥራዎች መልካም ቢኾኑም፣ በአግባቡ ካልተመሩ አደጋ ሊያመጡ እንደሚችሉ አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG