በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጸጥታ ችግር የታጎለው የሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት “እየተቆራረጠም ቀጥሏል”


በጸጥታ ችግር የታጎለው የሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት “እየተቆራረጠም ቀጥሏል”
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:05 0:00

በጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎቶች፣ በውስን ስምሪት እና በተቆራረጠ መልክም ቢኾን መቀጠሉን፣ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ተናገሩ።

በትግራይ ክልል ተጀምሮ ወደ አማራ እና አፋር ክልል የተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመጀመሩ ቀደም ብሎም ኾነ ከጦርነቱ በኋላ፣ በአገር ውስጥ የሚደረጉ የየብስ እንቅስቃሴዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት መታጎላቸውን፣ በተለያየ ጊዜ እና ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች አስተያየት የሚሰጡ ነዋሪዎች ሲናገሩ ቆይተዋል።

ወደ አንዳንድ አካባቢዎች በተሽከርካሪ መንቀሳቀስ አዳጋች በመኾኑም፣ ሰዎች የአየር ትራንስፖርት ለመጠቀም እንደሚገደዱ ይናገራሉ። ለመኾኑ በአኹኑ ወቅት ያለው የሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ምን ይመስላል?

ለዚኽና ለሌሎችም ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት፣ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩን አነጋግረናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG