በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት መሀል በሚጓዙ የሰሜን ወሎ ዞን መንገደኞች መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ


 በግጭት መሀል በሚጓዙ የሰሜን ወሎ ዞን መንገደኞች መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:55 0:00

በአገር መከላከያ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች የሚደረጉ የተኩስ ልውውጦች፣ ከደሴ ወደ ወልዲያ ከወልዲያ ወደ ደሴ በተሽከርካሪ ሲጓጓዙ በነበሩ ተሳፋሪዎች እንዲሁም በእግራቸው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ያልታጠቁ ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ማስከተሉን፣ የዐይን እማኝ መኾናቸውን የተናገሩ ግለሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ፡፡

አስተያየት ሰጭዎቹ፣ እልባት ያልተገኘለት የትጥቅ ግጭት በተሽከርካሪ በሚንቀሳቀሱ ተሳፋሪዎች ላይ የደኅንነት ስጋትም አስከትሏል፤ ብለዋል፡፡

ስለጉዳቱ ተጨማሪ ማብራሪያ ከወልዲያ ሆስፒታል፣ ከዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያና ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒከሽን ቢሮ ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም፡፡

XS
SM
MD
LG