No media source currently available
ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች፣ በህወሓት ታጣቂዎች ላይ የቀረበውን ክስ፣ እያጣራ መኾኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ቃል አቀባዩ ነብዩ ተድላ ዛሬ ኀሙስ በሰጡት መግለጫ፣ ጉዳዩን በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ እያጣራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ክሱን ማስተባበሉ ይታወቃል፡፡
አቶ ነብዩ በዛሬው መግለጫቸው፣ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የቪዛ አሰጣጥ ገደብ እንዲያነሣም ጠይቀዋል፡፡