በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥቃት ያሰጋቸው የሱዳን ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያ ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ


ጥቃት ያሰጋቸው የሱዳን ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያ ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:54 0:00

በሰሜን ጎንደር ዞን ከሚገኙት የኩመር እና አውላላ መጠለያ ጣቢያዎች፣ ከአንድ ሺሕ በላይ የሱዳን ስደተኞች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ፡፡ በመጠለያ ጣቢያው ተጠልለው የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ባጋጠመው የጸጥታ ችግር ምክንያት፣ ሱዳናውያኑ ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያዎቹ መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም፣ በስደተኞቹ ላይ ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር የሚመለከት መረጃ እንደደረሰው ገልጾ “ጉዳዩን እያጣራኹ ነው፤” ብሏል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በምኅጻሩ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር በበኩሉ፣ ከኩመር እና አውላላ የመጠለያ ጣቢያዎች ከ1ሺሕ300 በላይ የሱዳን ስደተኞች ለቀው መውጣታቸውን አስታውቋል፡፡ በመጠለያ ጣቢያዎቹ አካባቢ ያለው የጸጥታ ችግርም እንደሚያሳስበው ትላንት ባወጣው መገለጫ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG