ከዕድሜአቸው የበዛውን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሳለፉት ወ/ሮ ሊድያ ሸፈርድ ቤት ንብረታቸውን ሸጠው ትግራይ ውስጥ ለተወለዱበት መንደር ትምህርት ቤትና ክሊኒክ ሠርተዋል።
እርሣቸው ባሠሩት ትምህርት ቤት የተማሩ ከተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ዛሬ ማኅበረሰባቸውንም ሃገራቸውንም በተለያዩ መስኮች እያገለገሉ ናቸው።
የአሜሪካ ድምጿ ብርሃን ኃይሉ ወ/ሮ ሊድያን፣ ተማሪዎችን፣ የሁለቱንም ተቋማት ኃላፊዎች አነገጋራ ተከታዩን ዘግባለች።