በጋምቤላ ክልል፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ታጣቂዎች በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ፈጸሙት በተባለ ጥቃት፣ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም፣ የጥቃቱ ሰለባ የኾኑ ሰባት ቁስለኞችን እያከመ እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡
የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ በበኩሉ፣ የክልሉ መንግሥት አጥፊዎችን ለሕግ እንዲያቀርብ ጠይቋል፡፡
የክልላዊ መንግሥቱ፣ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ደግሞ፣ ጥቃት ፈጻሚዎችን ለመያዝ ክትትል እያደረገ እንደኾነ ገልጾ፣ ሕዝቡ በጥቆማ እንዲተባበረው ጥሪ አቅርቧል፡፡