በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመዳና ትልቁ ኮንሰርት በሪዮ ተካሄደ


መዳና በሪዮ ኮንሰርት ላይ (ፎቶ ሮይተርስ ግንቦት 5፣2024)
መዳና በሪዮ ኮንሰርት ላይ (ፎቶ ሮይተርስ ግንቦት 5፣2024)

“የፖፕ ሙዚቃ ንግሥት” በመባል የምትታወቀው መዳና፣ ኮፓካባና በተሰኘውና በሪዮ ዴ ጃኔሮ በሚገኘው የባህር ዳርቻ መዝናኛ ትላንት ቅዳሜ ነፃ የሙዚቃ ትርዒት አቅርባለች፡፡ የባህር ዳርቻውን ወደ ግዙፍ የዳንስ ወለል የቀየር ትርዒት ነው ተብሏል።

መዳና ትላንት ምሽት ያቀረበችው ኮንሰርት እስከ አሁን ካሳየችው ሁሉ ትልቁ ነው ተብሏል።

ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ “ሰለብሬሽን ቱር” ብላ የሰየመችውንና በመላው ዓለም ስታሳይ የከረመችውን ትርዒት፣ ብራዚል፣ ሪዮ ላይ አጠናቃለች፡፡

“በዓለም እጅግ ቆንጆ በሆነው ከተማ ተገኝተናል” ያለችው መዳና ወደ ባህሩ እንዲሁም “ክራይስት ዘ ረዲመር” ወይም ‘አዳኙ ክርስቶስ’ በመባል ወደሚታወቀውና ከተማዋን ወደታች ወደሚመለከተው ሃውልት ጣቷን በመጠቆም፣ “ይህ ቦታ ድንቅ ነው” ስትል ተደምጣለች፡፡

ተወዳጅ ዘፈኖቿን ያቀረበችው መዳና፣ ‘ሊቭ ቱ ቴል’ በተሰኘው ዜማዋ በኤድስ በሽታ ሕይወታቸውን ያጡትን ዘክራለች፡፡

ዝግጅቱን 1.6 ሚሊዮን ሰዎች እንደታደሙት የከተማዋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG