በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒዤር አዲስ ዙር የሩሲያ ወታደራዊ አማካሪዎችንና መሣሪያዎችን ተረከበች


 ኒዤር ከደረሱት የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላኖች አንዱ (ፎቶ ኤፒ ሚያዚያ 13፣ 2024)
ኒዤር ከደረሱት የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላኖች አንዱ (ፎቶ ኤፒ ሚያዚያ 13፣ 2024)

የአሜሪካ ኃይል እንዲወጣ በመጠየቅ ላይ ያለችው ኒዤር፣ አዲስ ዙር የሩሲያ ወታደራዊ አማካሪዎችን እና መሣሪያዎችን መቀበሏን የሃገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቭዥን አስታውቋል።

ኒዤር አንድ መቶ የሚሆኑ የሩሲያ የመጀመሪያው ዙር አማካሪዎችና የመከላከያ መሣሪያዎችን ከሶስት ሣምንታት በፊት መረከቧ ታውቋል።

ትላንት ቅዳሜ ደግሞ ሁለት ወታደራዊ አውሮፕላኖች መድረሳቸው ሲነገር፣ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ አማካሪዎችን እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን የጫኑ ሶስት ወታደራዊ አውሮፕላኖች ኒዤር ገብተዋል ተብሏል።

‘የአፍሪካ ቡድን’ የተሰኘው የሩሲያ ወታደራዊ አማካሪ ቡድን፣ የዋግነር ቡድን ተተኪ ተደርጎ የሚታይ ሲሆን፣ ሩሲያ እስከ አሁን ሶስት ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሙሉ መሣሪያና አማካሪዎችን መላኳን በቴሌግራም ላይ ባሰፈረው መልዕክት አስታውቋል። ትላንት ቅዳሜም ተጨማሪ አሰልጣኞች፣ መሣሪያዎች እና የምግብ ሸቀጦች መድረሳቸውን ገልጿል።

የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን ሐሙስ ዕለት እንዳስታውቁት፣ የሩሲይ ወታደሮች የአሜሪካንም ወታደሮች መሠረት የሆነውን የኒዤርን አየር ማረፊያ ተቆጣጥረዋል።

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ሥልጣን የጨበጠው ወታደራዊ ሁንታ፣ የፈረንሣይ ወታደሮችን ከሃገሪቱ አባሮ፣ የአሜሪካ ወታደሮችም ለቀው እንዲወጡ ጠይቋል።

አሜሪካ በዛች ሃገር የሚገኙ 1ሺሕ የሚሆኑ ወታደሮቿን ለማስወጣት ተስማምታለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG