በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዋይት ሃውስ የአጥር በር ጋራ የተጋጨው ሾፊር ሕይወቱ አለፈ


ፎቶ ኤፒ (ግንቦት 5፣ 2024)
ፎቶ ኤፒ (ግንቦት 5፣ 2024)

ትላንት ቅዳሜ በሃገሬው አቆጣጠር ግንቦት 4፣ 2024 ምሽት 10፡30 ሠዓት ላይ አንድ ሾፌር ከዋይት ሃውስ የውጪ አጥር በር ጋራ ተጋጭቶ ወዲያው ሕይወቱ እንዳለፈ፣ የፕሬዝደንታዊ ጥበቃ አገልግሎት ‘ሲክረት ሰርቪስ’ አስታውቋል።

በዋይት ሃውስ ላይ የተደቀነ አደጋ አለመኖሩን፣ በጥበቃ አሰራር ደንብ መሠረት መኪናውን መፈተሹን እንዲሁም ግለሰቡን ለማዳን ያደረገው ሙከራ ሞቶ በመገኘቱ እንዳልተሳካ፣ የጥበቃ አገልግሎቱ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ትላንት ማምሻውን ባሰፈረው መልዕክት አስታውቋል።

የፕሬዝደትንታዊ ጥበቃ አገልግሎት ከዋሽንግተን ዲሲ የእሳት አደጋ መከላከያና ፖሊስ ጋራ በመሆን ሞት ያስከተለውን የመኪና አደጋ በመመርመር ላይ መሆናቸውን የአገልግሎቱ ቃል አቀባይ አንተኒ ጉግሊያሚ አስታውቀዋል። በሕዝብም ሆነ በዋይት ሃውስ ላይ የተደቀነ አደጋ እንደሌለም ጨምረው አስታውቀዋል።

ባለፈው ጥር አንድ ግለሰብ በተመሳሳይ መኪናውን ከአጥሩ ጋራ ማጋጨቱን ተከትሎ፣ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር አውለውት ነበር ነበር።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ በዋይት ሃውስ ተመሳሳይ ድርጊት በመበርከቱ፣ ከአራት ዓመት በፊት ረዘም ያለ እና ጠንካራ የብረት እጥር እንዲሠራ አስገድዷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG