በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬኒያ ጎርፍ እና አውሎ ንፋስ ተባብሶ እንደሚቀጥል ፕሬዘዳንቱ አስታወቁ


የኬኒያ ጎርፍ ሚያዚያ 2016
የኬኒያ ጎርፍ ሚያዚያ 2016

የኬኒያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ባለፉት ሳምንታት በኬንያ ሰፊ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት ያስከተለው እንዲሁም ቢያንስ 210 ሰዎች የሞቱበት ከባድ ዝናብ በዚህ ወር ተባብሶ እንደሚቀጥል ትላንት ዐርብ ተናገሩ።

የጎርፍ አደጋው በምስራቅ አፍሪካ የትልቅ ምጣኔ ሀብት ባለቤት በሆነችው በኬንያ ቤቶችን፣ መንገዶችን፣ ድልድዮችን እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ወድሟል። ባለፈው አመት መጨረሻ በኤልኒኖ የአየር ሁኔታ ክስተት በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ጨምሯል።

ፕሬዘዳንት ሩቶ በኬንያ ቴሌቪዥን ቀርበው "በሚያሳዝን ሁኔታ ዝናቡና አውሎ ንፋሱ ይባባሳል ተብሎ ስለሚገመት የዚህን አስጊ ወቅት መጨረሻው ገና አላየንም። ኬንያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አውሎ ንፋስ ልትጋፈጥ ትችላለች" ብለዋል።

በኬንያ ደቡባዊ ጎረቤት በሆነችው ታንዛኒያ ቅዳሜ ዕለት ወደ ስምንት ሜትር ርቀት 165 ኪሎ ሜትር ከፍታ ያለው ማዕበል እንደሚመጣ የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና መተግበሪያ ማዕከል አስታውቋል።

በኬኒያ በዚህ ሳምንት ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የመጪው የትምህርት ዘመን እና የሁሉም ትምህርት ቤቶች ዳግም መከፈት በሌላ መግለጫ እስከሚገለጥ ድረስ መራዘሙን ሩቶ ተናግረዋል።

የናይሮቢ መንግስት በጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማስተናገድ ከለጋሽ እና ገባሬ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመስራት 115 መጠለያ ጣቢያዎች ለተጎጂዎች የምግብ እና የምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን ለማቅረብ እየሰራ ነው ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG