“ፕሬስ ለምድሪቱ የተፈጥሮ አካባቢ ቀውስ ባለበት ዓለም ጋዜጠኝነት” የሚል መርህ የተሰጠው የዘንድሮው የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ የአካባቢ ቀውስ አንፃር ለጋዜጠኝነት እና ሐሳብን በነጻነት ለመግለጽ አስፈላጊነት የተሰጠ ነው።
ግጭቶች በበረከቱባት ዓለም ያለፈው ዓመት ለጋዜጠኞች የከፋ እንደነበር ያመላከቱት ሪፖርቶች፣ ጦርነት እየተካሄዱ ያሉባቸውን እና ለሕይወት እጅግ እደገኛ የሆኑ አካባዎችን ጨምሮ የመገናኛ ብዙኃን አባላት በዓለም ዙሪያ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እየሰሩ መሆናቸውን ለጋዜጠኞች ደሕንነት የቆሙ ዓለም አቀፍ የመብት ድርጅቶች ጠቁመዋል።
ዕለቱን ምክኒያት በማድረግ፡ ዋና መሥሪያ ቤቱን በኒውዮርክ ያደረገውን የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሲፒጄን የአፍሪቃ ፕሮግራሞች ኃላፊ አንጄላ ኩዊንታልን አነጋግረናል ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።