በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በተማሪዎች የምግብ በጀት እጥረት የወላይታ ሶዶ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ውዝግብ


በተማሪዎች የምግብ በጀት እጥረት የወላይታ ሶዶ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ውዝግብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:36 0:00

የወላይታ ሶዶ እና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የሚቀርብላቸው ምግብ፣ በዐይነትም በመጠንም በጥራትም ከጊዜ ወደ ጊዜ መቀነሱን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ በትምህርታቸው ላይም አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩንም አመልክተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ፣ ባለፈው ሳምንት በተናጠል በየግቢያቸው በለጠፏቸው ማስታወቂያዎች፣ ለተማሪዎች ምግብ የሚያቀርቡበት

በጀት ማለቁን አስታውቀዋል፡፡

በአንጻሩ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች፣ የበጀት እጥረት አላጋጠመንም፤ ችግር ቢኖር እንኳን ከፌደራል መንግሥት እየጠየቅን እየቀረበልን ነው፤ ሲሉ የተማሪዎቹን አቤቱታ አስተባብለዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ፣ ለተማሪዎቻችን በቂ ምግብ እና አገልግሎት እያቀረብን ነው፤

ተረጋግተው እየተማሩ ነው፤ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG