በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የተራዘመ የትምህርት መቋረጥ ለማኅበራዊ ቀውስ እያጋለጠ ነው


በአማራ ክልል የተራዘመ የትምህርት መቋረጥ ለማኅበራዊ ቀውስ እያጋለጠ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:03 0:00

በአማራ ክልል ግጭት በቀጠለባቸው አካባቢዎች ለዘጠኝ ወራት ያህል ትምህርት በመቋረጡ፣ በተማሪዎች ላይ ያለዕድሜ ጋብቻን ጨምሮ ለሌሎች ማኅበራዊ ቀውሶች ሊዳርጉ የሚችሉ ጎጂ ልማዶችን እያስከተለ እንደኾነ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ወላጆች እና መምህራን እንዲሁም የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በምኅጻሩ ዩኤን-ኦቻ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ ባወጣው መግለጫ፣ በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት እና በፊተኛው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት፣ እ.አ.አ እስከ ሚያዝያ ወር መጀመሪያ በነበረው ጊዜ፣ 4ሺሕ178 ትምህርት ቤቶች ተዘግተው መቆየታቸውን ገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG