በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሕዝብ የኀይል አማራጭ ፈላጊዎችን ወደ ሰላም እንዲያመጣ ተመስገን ጥሩነህ ጠየቁ


 ሕዝብ የኀይል አማራጭ ፈላጊዎችን ወደ ሰላም እንዲያመጣ ተመስገን ጥሩነህ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00

በትግራይ ክልል፣ “ችግሮችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ የኀይል አማራጭን መጠቀም የሚፈልግ ከሕዝቡ ያፈነገጠ አስተሳሰብ ያለው አካል አለ፤” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ሕዝቡ ይህ አካል ወደ ሰላም እንዲመጣ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ጥሪ አቀረቡ፡፡

አቶ ተመስገን፣ በአማራ ክልል የተለያዩ ጥያቄዎች አሉን ብለው መብታቸውን ለማስከበር ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኀይሎች፣ የተወለዱበትን ማኅበረሰብ ልማት በከፍተኛ ሁኔታ ከመጉዳት ውጪ ሌላ ዓላማ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

ባለፉት ሁለት ቀናት፣ ሚያዝያ 19 እና 20 ቀን 2016 ዓ.ም.፣ ከክልል እና ከፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋራ በመኾን በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የልማት ጉብኝት ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ከጉብኝታቸው በኋላ በምስል በሰጡት እና በመሥሪያ ቤታቸው ፌስቡክ ገፅ ላይ በተላለፈው መልዕክት፤ ችግሮች በውይይት እንጂ በጠመንጃ የሚፈቱበት አቅጣጫ ማብቃት እንዳለበት ተናግረዋል።

ይህ ካልኾነ ግን፣ የፌደራሉ መንግሥት ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንደሚወጣ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ አሳስበዋል፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት አስተያየት ላይ፣ ከህወሓት እና በአማራ ከልል ከሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች ቡድን፣ በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የልማት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝቷል።

XS
SM
MD
LG