በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ ጎርፍ ሕይወት መቅጠፉን ቀጥሏል


ፎቶ ኤፒ (ሚያዚያ 12፣ 2024)
ፎቶ ኤፒ (ሚያዚያ 12፣ 2024)

በኬንያ እየቀጠለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከተለው ጎርፍ ሕይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥር 76 መድረሱ ተነግሯል። ካለፈው ወር ጀምሮ እየጣለ ያለው ዝናብ እንደሚቀጥል እና ሕዝቡ ለበለጠ ከባድ ዝናብ እንዲዘጋጅ ባለሥልጣናት አሳስበዋል።

በትላንትናው ዕለት ብቻ ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተነግሯል።

‘ኤል ኒኞ’ በተሰኘው የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ በኬንያና በበአካባቢው ሃገራት ዝናብ በከፍተኛ መጠን በመጣል ላይ ይገኛል።

በመዲናዋ ናይሮቢ 130 ሺሕ ሰዎች መፈናቀላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። የ24ሺሕ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ታውቋል።

መዲናዋ ናይሮቢ ከባድ ጉዳት የታየባት ሆናለች፡፡ ከሟቾቹ ውስጥ 32 የሚሆኑት የከተማዋ ነዋሪዎች ናቸው። ከ16ሺሕ በላይ ቤተሰቦችም ተፈናቅለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG