በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቶጎ የፓርላማ ምርጫ ልታደርግ ነው


የቶጎው ፕሬዝደንት ፎ ኛሲምቤ (ፋይል ፎቶ፣ ኤፒ መጋቢት 30፣ 2024)
የቶጎው ፕሬዝደንት ፎ ኛሲምቤ (ፋይል ፎቶ፣ ኤፒ መጋቢት 30፣ 2024)

አጨቃጫቂ የነበረውን የሕገ መንግስት ማሻሻያ ተከትሎ፣ ቶጎ ነገ ሰኞ ሚያዚያ 21፣2016 የፓርላማ ምርጫ ታደርጋለች፡፡ ሕገ መንግስታዊ ማሻሻያው ፕሬዝደንት ፎ ኛሲምቤ ለረጅም ዘመን ቤተሰባቸው ይዞ የነበረውን አገዛዝ የሚያራዝም ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ይከሳሉ።

ለሃያ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት ፎ ኛሲምቤ፣ ሥልጣኑን የተረከቡት ከአባታቸው ኛሲምቤ ኢያዴማ ነው። አባታቸው ለዓርባ ዓመታት ለሚጠጋ ዘመን ቶጎን ገዝተዋል።

የሕገ መንግስታዊ ማሻሻያው ምዕራብ አፍሪካዊቷን ሃገር በአንድ ቤተሰብ ቁጥጥር ሥር እንድትቀጥል ያደርጋል ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ።

በማሻሻያው መሠረት ፕሬዝደንቱ በሕዝቡ ሳይሆን በፓርላማው ይመረጣል። የአብላጫ ድምፅ ያለው ፓርቲ መሪ የሚኒስትሮች ም/ቤት ፕሬዝደንት ሲሆን፣ ዋናው ሥልጣንም የዚሁ ም/ቤት ይሆናል ተብሏል።

ገዢው ፓርቲ ‘ዩኒየን ፎር ዘ ሪፐብሊክ’ በሰኞው ምርጫ አሸናፊ ከሆነ፣ ኛሲምቤ ሥልጣናቸውን እንደተቆናጠጡ ይቀጥላሉ ተብሏል። በማሻሻያው መሠረትም የሥልጣን ዘመን ገደቡ አይመለከታቸውም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG