በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ስምንት የምርመራ ቀናትን ፈቀደ


በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ስምንት የምርመራ ቀናትን ፈቀደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:55 0:00

በአገራዊ ምክክሩ ለሚሳተፉ የታጠቁ ኀይሎች የደኅንነት ጥበቃ እንደሚደረግ ኮሚሽኑ አስታወቀ

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሴሊያዊ የክፍያ ሰነድ ጋራ ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌሎች የባንክ ሒሳቦች 6ሚሊዮን 50ሺሕ ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሞክረዋል፤ በሚል ነበር ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡

በአፍሪካ ኅብረት የጸጥታ ሠራተኞች ተይዘው ለፌደራል ፖሊስ ተላልፈው መሰጠታቸውና ተጠርጣሪው፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው፣ የሰባት ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ተፈቅዶባቸው እንደነበር የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኅን ዘግበዋል።

በዛሬው ችሎት መርማሪ ፖሊስ ያከናወናቸውን ሥራዎች ለችሎቱ ያስረዳ ሲኾን፣ በስድስት ጠበቆች ተወክለው የቀረቡት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በበኩላቸው፣ በቦታው ላይ ከመገኘት በቀር የፈጸሙት ወንጀል አለመኖሩን በመጥቀስ የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡

ፖሊስ፣ ተጠርጣሪዎቹ ቢወጡ ማስረጃ ሊሰወር ይችላል በሚል የዋስትና ጥያቄአቸውን ተቃውሟል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ፣ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የስምንት ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

የዛሬውን የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ውሎን በተመለከተ ከጠበቆቻቸው አንዱ ቱሊ ባይሳ ጋራ አስማማው አየነው ያደረገውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG