በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አበባ የደንጊያ እና አፈር ክምር ተንዶ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ


በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 “ጠሮ መስጂድ” አካባቢ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ ሰዎች ተሰባስበው። ፎቶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ስክሪን ቅጂ።
በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 “ጠሮ መስጂድ” አካባቢ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ ሰዎች ተሰባስበው። ፎቶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ስክሪን ቅጂ።

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 “ጠሮ መስጂድ” አካባቢ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ሚያዝያ 16 ንጋት 11 ሰዓት ላይ፣ ለቤት ግንባታ የተከመረ ደንጊያ እና አፈር ተንዶ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የሰው ሕይወት የጠፋበትን ድንገተኛ አደጋ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ መጀመሩን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ያገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ ብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ እንደዘገበው፣ ጠሮ መስጂድ አካባቢ እየተገነባ ላለ ቤት የተከመረ ደንጊያ እና አፈር ተንዶ በአቅራቢያው ባለ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ፣ በቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩ የሰባት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው መድረሱን ለአሜሪካ ድምፅ ያረጋገጡት የአዲስ አበባ የፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ የሰው ሕይወት የጠፋበት ድንገተኛ አደጋ ምርመራ ገና እየተጣራ እንደኾነ ገልጸዋል። በአደጋው አንድ ሕጻንን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል።

ለምርመራው ሲባል ኹሉንም መረጃዎች አሁን ግልጽ ማድረግ እንደሚያስቸግር የተናገሩት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ ወደፊት ፖሊስ ኹኔታውን እያየ፣ የተያዙትንና ከጉዳዩ ጋራ ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን ጨምሮ የምርምራውን ውጤት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG