በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባ ቀደምት ሰፈሮች ፈረሳ ለጸጸት እንደሚዳርግ ታዋቂው አርክቴክት አሳሰቡ


የአዲስ አበባ ቀደምት ሰፈሮች ፈረሳ ለጸጸት እንደሚዳርግ ታዋቂው አርክቴክት አሳሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:27 0:00

የአዲስ አበባ ቀደምት ሰፈሮች በግንዛቤ እጥረት እየፈረሱ እንደኾነ የገለጹት ታዋቂው አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ፣ ለጸጸት ከመከተሉ በፊት ሳይፈርሱ የቀሩ ቅርሶችን ለማዳን መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥ ጠየቁ፡፡

አርክቴክቱ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ፣ በታሪካዊ ሕንፃዎች የጥገና ዲዛይን ሥራ የሚታወቁት አርክቴክት ፋሲል፣ በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉት የልማት ሥራዎች ተገቢነት ቢኖራቸው እንኳን፣ ለቅርሶች ጥበቃ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋም፣ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ባለው የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ፣ ከከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋራ ባለፈው ሳምንት መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG