በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእንግሊዝ ፓርላማ የሩዋንዳ ጥገኝነት ሕግ አፀደቀ


የእንግሊዝ ፓርላማ የሩዋንዳ ጥገኝነት ሕግ አፀደቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:56 0:00

የእንግሊዝ ፓርላማ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የተያዘውን እቅድ መጀመር የሚያስችለውን ረቂቅ ሕግ ማክሰኞ ዕለት አፅድቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክም፣ በሚቀጥሉት ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ባለው ጊዜ፣ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀምሩ ቃል ገብተዋል።

ሱናክ አክለው መንግሥት የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችን መከራየቱን እና ስደተኞቹን ወደ ሩዋንዳ የሚወስዱ ሠራተኞች ማሰልጠኑን የገለፁ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት መጨረሻ ከሚካሄደው ምርጫ በፊት የዚህ ፖሊሲ ተፈፃሚ መሆን፣ ወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው የተሻለ እድል እንዲኖረው ያደርጋል የሚል ተስፋ አላቸው።

የእንግሊዝ ፓርላማ፣ ለረጅም ጊዜ፣ የስደተኞቹን ደህንነት ለማስጠበቅ ተጨማሪ እርምጃዎች ሳይወሰዱ አጨቃጫቂ የነበረውን ረቂቅ ሕግ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር። ሆኖም ሱናክ ሕጉ እስኪፀድቅ ድረስ፣ መንግሥታቸው ፓርላማው እስከ ሰኞ ምሽት ስብሰባውን እንዲቀጥል እንደሚያስገድድ ከገለፁ በኋላ፣ ተቃውሞው እየላላ መጥቶ ሕጉን አፅድቋል።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከእስያ ጦርነት እና ድህነት የሚሸሹ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ እንግሊዝ ገብተዋል። ስደተኞቹ ወደ እንግሊዝ የሚያቀኑት ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በሚያዘጋጇቸው ትንንሽ ጀልባዎች አማካኝነት በደቡባዊ እንግሊዝ እና በሰሜናዊ ፈረንሳይ መካከል ያለውን የአትላንቲክ ውቅያኖስ መተላለፊያ አቋርጠው ነው።

መንግሥት ስደቱን ማስቆም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ቢሆንም፣ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሀገር ውስጥ ከማስተናገድ ይልቅ ሰዎችን ወደ ሩዋንዳ መመለሱ ኢ- ሰብአዊነት ነው ሲሉ ተቺዎች ይከራከራሉ። ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር በራሷ ያላትን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በመጥቀስም፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች አደጋ ሊደርስባቸው ወደሚችልበት የትውልድ ሀገራቸው ሊመለሱ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG