በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬኒያውያንና ኢትዮጵያውያን በለንደኑ ማራቶን ድል ቀናቸው


ኬኒያውያንና ኢትዮጵያውያን በለንደኑ ማራቶን ድል ቀናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:09 0:00

ኬኒያውያንና ኢትዮጵያውያን በለንደኑ ማራቶን ድል ቀናቸው

ከዓለማችን ግዙፍ የጎዳና ላይ ስፖርታዊ ትዕይንቶቸ መካከል አንዱ የኾነው የ"ለንደን ማራቶን" በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ተካሒዷል።

በሁለቱም ጾታዎች ምድብ የተደረጉ ውድድሮችን፣ ኬኒያውያን አትሌቶች በቀዳሚነት ሲያጠናቅቁ፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በወንዶች ምድብ፣ ኬኒያዊው አሌክሳንደር ሙቲሶ፣ 42 ኪ.ሜ. የሚርዝመውን ጎዳና 2:04:01 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ አሸንፏል። 14 ሰከንዶች ያህል ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ያገኘው ኢትዮጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ነው። እንግሊዛዊው ኤሚል ኬረስ፣ ከቀዳሚው ሰዓት በ2 ደቂቃ ከ45 ሰከንዶች ዘግይቶ በመግባት ሦስተኛ ኾኖ አጠናቋል።

በሴቶች ምድብ፣ ኬኒያዊቷ ፔሪስ ጂፕቺርቺር፣ ውድድሩን 2:16:16 በማጠናቀቅ አሸንፋለች፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ትዕግሥት አሰፋ፣ ከሰባት ሰከንዶች በኋላ የውድድሩን ማጠናቀቂያ መሥመር በማለፍ የሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ጆስሊን ጂፕኮሲጌ፣ ትዕግስት አሰፋን በአንድ ሰከንድ ተከትላ በመግባት ከፍተኛ ፉክክር የታየበትን ውድድር በሦስተኛነት አጠናቃለች።

ባልደረባችን ኤቢሳ ነገሰ፣ ለንደን ላይ ለአሸናፊነት ከበቁት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቀነኒሳ በቀለ እና ትዕግሥት አሰፋ ጋራ አጭር ቆይታ አድርጓል።

ናዝሬት ወልዱ እና ጫላ ረጋሳ የቬና ማራቶንን አሸነፉ

ወደ ሌላ አትሌቲክስ ተኮር ዜና ስንሻገር፣ ኢትዮጵያዊው ጫላ ረጋሳ እና ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱ፣ ትላንት የተካሔደው የ41ኛው የቬና ከተማ ማራቶን ውድድር አሸናፊዎች ኾነዋል፡፡

ጫላ ረጋሳ፣ ውድድሩን 2:06:35 በኾነ ሰዓት በማጠናቀቅ በርቀቱ ታሪክ ሦስተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል። ኬንያውያኑ በርናርድ ሙዬ እና አልበርት ካንጎጎ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል። በርናርድ ውድድሩን 2:10:42 ሲያጠናቅቅ፣ አልበርት ደግሞ በሁለት ሰከንዶች ዘግይቶ በመግባት ከአሸናፊዎች ተርታ ኾነዋል፡፡

በሴቶች ውድድር፣ ናዝሬት ወልዱ በኤርትራ የአትሌቲክስ ውድድር ታሪክ በቀዳሚነት በተመዘገበው 2:24:08 ሰዓት በመግባት አሸናፊ ኾናለች። ናዝሬት ያስመዘገበችው ሰዓት፣ በፓሪስ በሚካሔደው ኦሎምፒክ ላይ ለመሳተፍ ያስችላታል።

በለንደኑ ማራቶን የመጀመሪያ ውድድሯን ያደረገችው ኬኒያዊቷ አዲስ ተወዳዳሪ ፌዝ ቺፕኮች፣ 2:26:22 በኾነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ደረጃዋን አስጠብቃለች። የአገሯ ልጅ ሬቤካ ታንዊ ደግሞ፣ ውድድሩን 2:26:53 በኾነ ሰዓት በማጠናቀቅ የሦስተኛ ደረጃን ይዛለች።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለአምስት ዓመታት ከውድድር ታገደች

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል ለሦስት ሺሕ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር የደረሰችው ዘርፌ ወንድማገኝ፣ የተከለከሉ አበረታች ንጥረ ነገሮችን መውሰዷ በምርመራ በመረጋገጡ፣ ለአምስት ዓመታት ከውድድሮች መታገዷን የ“አትሌቲክስ ታማኝነት ተቋም” ይፋ አድርጓል።

አትሌቷ፣ ከዓመት በፊት በዓለም ሻምፒዮና ላይ ለጥቂት የቀዳሚነት ደረጃን ማጣቷ ይታወሳል፡፡

በአትሌት ዘርፌ ደም ውስጥ፣ የኦክስጂን ዝውውርን የሚያፋጥን ቴስቴስትሮንና የሌላ ንጥረ ነገር ናሙናዎች ከተገኙ በኋላ የፀረ አበረታች ሕጎችን መጣሷን ማመኗን፣ ተቋሙ ባተመው ውሳኔ ላይ ጠቅሷል። ንጥረ ነገሮቹ፥ የደም ማነስ እና የኩላሊት ሕመሞችን ለማከም ለአትሌቷ የተሰጡ መኾናቸውን የሚያብራራ የሐኪም ምስክርነት ለተቋሙ በኤሜይል ደርሶታል፡፡ ኾኖም አትሌቷ፣ የፀረ አበረታች ሕጎችን በመጣሷ ረገድ የአቋም ለውጥ እንደማያደርግ አስታውቋል። ተቋሙ አክሎም፣ የአትሌቷን ፊርማ የያዘ የእምነት ማረጋገጫ ባለፈው ሳምንት መቀበሉን ገልጿል።

በተመሳሳይ ተቋሙ፣ “የቴስቴስትሮን ንጥረ ነገር በምርመራ አገኘኹባት” ባላት እ.እ.አ የ2022 የሦስት ሺሕ ሜትር መሰናክል ቻምፒዮን ኬንያዊቷ ሰልሊስቲን ቺፕቺርቺር ላይ፣ በዛሬው ዕለት የሦስት ዓመት የውድድር ተሳትፎ ክልከላ ውሳኔ አስተላልፏል። ዘገባው የአሶሼትድ ፕረስ ነው፡፡

/ሙሉውን የስፖርት ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG