በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስራኤል ጥቃት በርካቶች ተገደሉ


እስራኤል በራፋ ካደረሰችው ድብደባ በከፊል የሚያሳይ (ፎቶ ኤኤፍፒ ሚያዚያ 21, 2024)
እስራኤል በራፋ ካደረሰችው ድብደባ በከፊል የሚያሳይ (ፎቶ ኤኤፍፒ ሚያዚያ 21, 2024)

እስራኤል ማምሻዉን በራፋ ባደርሰችው የአየር ጥቃት 18 ሲገደሉ፣ 14 የሚሆኑት ሕፃናት እንደሆኑ ተዘግቧል።

በኩዌት ሆስፒታል አቅራቢያ በደረሰው ጥቃት ባልና ሚስት እንዲሁም የሶስት ዓመት ልጃቸው ተገድለዋል። ሃኪሞች የነፍሰ ጡሯን ጽንስ ማዳናቸው ተነግሯል።

በሌላ የአየር ጥቃት ደግሞ፣ 13 ሕፃናትና ሁለት ሴቶች መገደላቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

በሌላ በኩል እስራኤል በዌስት ባንክ ባደረሰችው ጥቃት 13 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የእስራኤል እና የፍልስጤም ኃይሎች ትላንት ቅዳሜ አስታውቀዋል።

ኑር ሻምስ በተሰኘው የስደተኞች ጣቢያ ላይ ከዓርብ ጀምሮ በተደረገ ዘመቻ፣ እስራኤል አስር የሚሆኑ እና “ሽብርተኞች” ብላ የገለፀቻቸውን ሰዎች “አስወግጃለሁ” ብላለች፡፡ ‘የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ’ የተባለው ቡድን ሦስት ዓባላቱ እንደተገደሉበት አስታውቋል። በጥቃቱ አንድ ታዳጊ መገደሉን የፍልስጤም ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ከግብጽ ጋራ በምትዋሰነው የራፋ ከተማ ከምታደርገው ጥቃት እስራኤል እንድትቆጠብ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በመጠየቅ ላይ ነው። እስራኤል በራፋ ላይ የምድር ጥቃት ለማድረግ ስትዝት ብትቆይም፣ እስከ አሁን ግን ወደ ተግባር አልገባችም።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ በራፋ የሚደረግን ማንኛውም ከፍተኛ ዘመቻ የባይደን አስተዳደር እንደማይደግፍ ባለፈው ዓርብ ከቡድን ሰባት ስብሰባ ጎን ለጎን በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG