በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን እና ትረምፕ የዩክሬን ጦርነት እንዴት ያብቃ በሚለው ይለያያሉ


ባይደን እና ትረምፕ የዩክሬን ጦርነት እንዴት ያብቃ በሚለው ይለያያሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:29 0:00

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ሁለት ዓመት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራትና እና ሪፐብሊካን ምክርቤት አባላት መካከል ወታደራዊ ርዳታን ወደ ኪቭ በመላክ ጉዳይ ላይ፣ ልዩነቶች ተፈጥረዋል።

ሁለቱ የፓርቲዎቹ ግንባር ቀደም ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች፣ በዩክሬን ባለው የሩሲያ ጦርነት አያያዝ የሚለያዩበትን መንገድ ያስረዳሉ። ለሁለት ዓመታት በዩክሬን የሚካሄደው ሁሉን አቀፍ ጦርነት ቀጥሏል።

በዚህ ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬን የሩስያ ሚሳይል ጥቃቶችን የሚመክቱ (HAWK የተባሉ) 138 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የተሻሻሉ የአየር መከላከያ መሳሪያዎችን ሽያጭ አጽድቃለች።

ፕሬዚዳንት ባይደን ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመቋቋም የዩናይትድ ስትቴስን ድጋፍ እንደምትሻ የአሜሪካን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ባለፈው ወር ባሰሙት ንግግራቸው "በዚህ ክፍል ውስጥ ያለ ማንም ሰው ፑቲን በዩክሬን ያቆማሉ ብሎ የሚያስብ ከሆነ፣ በእርግጠኝነት እንግራችኋለሁ አያቆሙም!። ከዩክሬን ጋራ ከቆምን እና ራሷን እንድትከላከል አስፈላጊውን መሳሪያ ካቀረብንላት ዩክሬን ፑቲንን ልታቆም ትችላለች ።” ብለዋል፡፡

ወረራው ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የባይደን አስተዳደር፣ በሩሲያ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጥሏል፡፡ ለዩክሬን የ75 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ ልኳል።

እንደ ዩክሬን ልጅነታቸው ስደተኛው ስቲቭ ካሳሊዝ "ለእኔ እንደ አለመታደል ሆኖ እዚያ ያለውን ጦርነት መመልከቱ፣ፑቲንን እና ሕዝቡን መመልከት፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቢያንስ በስሜት ማበራቸውን መመልከት በጣም አስፈሪ ነው" በማለት ድምጻቸውን ለባይደን እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን እና በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ትረምፕ ተገናኝተው ነበር፡፡

“ከእርስዎ ጋራ በመሆኔ ክብር ይሰማኛል አመሰግናለሁ፡፡” ለሚለው የትረምፕ ንግግር “በጣም አመሰግናለሁ፡፡” ሲሉ መለሱ ፑቲን፡፡ በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ዶናልድ ትረምፕ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋራ የነበራቸውን የቅርብ ግንኙነት ጠብቀዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በኋላም ዩክሬንን በመውረራቸው “ብልህ” ሲሉ ጠርተዋቸዋል፡፡

ዋሽንግተን ፖስት ትረምፕ ዩክሬን መሬት ለሩሲያ እንድትሰጥ ግፊት በማድረግ ጦርነቱን እንደሚያቆሙ ዘግቧል። የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ያንን “ኋላቀር ሐሳብ” ብለውታል።

ትረምፕ በቅርቡ በተካሄደ የምርጫ ቅስቀሳቸው ላይ ለዩክሬን በሚከፈለው የኔቶ መዋጮ ወደ ኋላ ቀርቷል ካሉት የአንድ ሀገር መሪ ጋራ ያደረጉትን ምልልስ በማስታወስ “እንግዲህ እንዳሉት ካልከፈልንና በሩሲያ ከተጠቃን ትከላከሉልናላችሁ?” ሲሉኝ “አያይ አልከላከልላችሁም፡፡ እንዲያውም እነሱ ያሻቸውን እንዲያደርጉ አበረታታቸዋለሁ፤ አልኳቸው” ብለዋል፡፡

ባይደንና ትረምፕ የዩክሬን ጦርነት እንዴት ማስቆም ይቻላል በሚለው ላይ በእጅጉ ይለያያሉ። እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2024 ዓ.ም የትረምፕ ቃል አቀባይ የነበሩት ካሮሊነ ሌቪት “ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለአሜሪካ ህዝብ ቃል ገብተዋል፡፡ ስለዚህ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም ሁለቱም ወገኖች የሰላም ስምምነት እንዲደራደሩ ማድረግ ይችላሉ ብለው ሊያምኑ ይችላሉ" ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

የኒው ሀምፕሻየር መራጩ አይዛክ ጊር “ከየትኛውም የውጭ ጦርነቶች እንድንርቅ፣ ወታደራዊ ወጪያችን እንዲቀንስ እና ወታደሮቻችንን ወደ ቤት እንዲመለሱልን ወይም ቤታቸው እንዲቆዩ ማድረጉ ለእኔ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።” ሲሉ ድምጻቸውን ለትረምፕ እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለዩክሬን እንዲላክ የቀረበው የ60 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ርዳታ ረቂቅ ውሳኔ ሳያገኝ በምክር ቤቱ ውስጥ ይገኛል፡፡

XS
SM
MD
LG