የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የመጀመሪያው የወንጀል ችሎት፣ ዛሬ ሰኞ፣ በኒውዮርክ ከተማ ተጀምሯል።
እ.ኤ.አ. በ2006 ከወሲብ ፊልም ተዋናይ ስቶርሚ ዳኒኤልስ ጋራ የነበራቸውን ግንኙነት ለመደበቅ በሰጡት የ“አፍ ማስያዥ” ገንዘብ ጋራ ማጭበርበር ፈጽመዋል በሚል የተከሰሱት ዶናድል ትረምፕ ጉዳይ የሚጀመረው፣ ከሕዝብ የሚውጣጡ ዳኞችን በመምረጥ ነው። በሌላ በኩል፣ ለዳግም ምርጫ
የሚወዳደሩት ፕሬዚዳንት ባይደን ደግሞ፣ በፔኒሲልቪኒያ ክፍለ ግዛት የምረጡኝ ዘመቻ ቅሰቀሳቸውን ያካሒዳሉ።
የቪኦኤ ዘጋቢ ቪሮኒካ ባልደራስ ኢግሊሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።