በሰሜናዊ ናይጄሪያ፣ የሽብርተኛው እስላማዊ ቡድን ቦኮ ሐራም ታጣቂዎች፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪ ልጃገረዶችን ከጠለፉ ዐሥር ዓመታት ተቆጠሩ፡፡
ከዚያ ወዲህ ብዙዎቹ ተጠላፊዎች ራሳቸው ከጠላፊዎቻቸው እጅ አምልጠዋል ወይም የጸጥታ ኀይሎች አስለቅቀዋቸዋል፡፡ 82 ልጃገረዶች ግን አሁንም በጠላፊዎቻቸው ቁጥጥር ሥር ናቸው፡፡
የልጃገረዶቹ ዕጣ ፈንታ፣ በአንድ ወቅት ጠንካራ በነበረው “ልጃገረዶቻችንን እናስለቅቅ” ከተባለ ተሟጋች ቡድን ዳግም ማንሰራራት ጋራ ተቆራኝቷል፡፡
በወቅቱ የቡድኑ እንቅስቃሴ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት አግኝቶ እንደነበር ያወሳው ቲመቲ ኦቢዬይዙ ከአቡጃ ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።