የኢራን የክቡር ዘብ አባላት ከሄሊኮፍተር በመውረድ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል በማለፍ የነበረች እና ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው ኮንቴነሮችን የጫነ መርከብን ዛሬ ቅዳሜ ተቆጣጥረዋል።
እስራኤል በሶሪያ 12 ሰዎችን የገደለችበትን ክስተት ተከትሎ መካከለኛው ምስራቅ እና ኳድ የተሰኘው የኢራን ከፍተኛ ዘብ ተጓዥ ሃይልን ጨምሮ የኢራንን የበቀል ጥቃት በተጠንቀቅ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
በኢራን መንግስት የሚደገፈው ኢርና የዜና አውታር የኢራን ዘብ ልዩ ሃይሎች የፖርቹጋል ባንዲራ የምታውለበልበውን እና በለንደን ከሚገኘው ዞዲያክ የባህር ሃይል ጋር ግንኙነት ያላትን ኤም.ኤስ.ሲ ኤሪስ የተሰኘችውን እቃ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ዘግቧል።
ዞዲያክ የባህር ሃይል የእስራኤላዊው ቢሊዬኔር ኤያል ኦፈር ዞዲያክ ግሩፕ ንብረት ነው። በጉዳዩ ላይ ዞዲያክ አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ተቀማጭነቱን በጄኔቫ ያደረገው ኤም.ኤስ.ሲ በመርከቡ ላይ 25 ሰራተኞች እንደነበሩ ቆይቶ አስታውቋል። ኢርና የዜና አውታር መርከቧ ወደ ኢራን የባህር ቀጠና እንደምትወሰድ ጨምሮ ዘግቧል።
መድረክ / ፎረም