ገለልተኛ የሆነ አንድ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን 50 ሺህ የሚሆኑ የሩሲያ ጦር አባላት፤ ሩሲያ ከሁለት ዓመት በፊት በሙሉ ሃይሏ ዩክሬንን ከወረረችበት ጊዜ አንስቶ መሞታቸውን እና አሃዙ ከዚህ በብዙ አስር ሺህዎች ሊልቅ እንደሚችል አስታውቋል።
ሚዲያዞና የተሰኘው እና ከቢቢሲ የዜና አውታር ጋር በመሆን የሞቱ የሩሲያ ወታደሮችን አሃዝ የሚከታተለው ይኸው ተቋም እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከጎሮጎርሳዊያኑ የካቲት 2022 አንስቶ 50,471 የሩሲያ ወታደሮች ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል። ሚዲያ ዞና አክሎም በሩሲያ የወታደር ቤተሰቦች መካከል ከ85,000 ሺህ በላይ የሚሆኑ የውርስ ሽግግሮች መደረጋቸውንም እና በተጨማሪም ሩሲያ በሳምንት 1,200 ወታደሮችን እያጣች መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል።
የዩክሬን ወታደራዊ ሃይል 451,730 የሩሲያ ወታደሮች በሞት እና በጉዳት ተገልለዋል በማለት ያስታወቀ ሲሆን ይሁን እንጂ የዩናይትድ ስቴትስ እና የብሪታኒያ የደህንነት ተቋማት ሩሲያ 300,000 ሞት እና ጉዳቶች ነው የደረሰውባት ሲሉ አስታውቀዋል።
ሩሲያ የሞቱ እና ጉዳት የደረሰባቸውን ወታደሮቿን አሃዝ እምብዛም በይፋ የማስታወቅ ልማድ የላትም። በሌላ በኩል ዩክሬን ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ 31,000 ወታደሮቼን አጥቻለሁ ብላለች።
መድረክ / ፎረም