በአሜሪካ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው በአንድ ወቅት፣ ከአመጋገባቸው ጋራ ለተያያዘ ከባድ የጤና ችግር ይጋለጣሉ።
በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ጊዜም፣ የሕክምና ርዳታ ያስፈለጋቸው ሰዎች ቁጥር ጨምሮ ነበር።
ይኹን እንጂ፣ ነጭ ባልኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚከሠት ከአመጋገብ ጋራ ተያያዥ የኾነ የጤና ችግር፣ በቂ ትኩረት አይሰጠውም፡፡ የፒ ቢ ኤስ ኒውስአወር ፕሮግራም ዘጋቢዋ አምና ናዋዝ ያጠናቀረችው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡