በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳ እንዲቆም ፓርቲዎች አሳሰቡ


ግጭት ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳ እንዲቆም ፓርቲዎች አሳሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:31 0:00

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ፈራሚ አካላት፣ ግጭት ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳን በማቆም ለስምምነቱ ተገዢ ሊኾኑ እንደሚገባ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳስበዋል፡፡

የአረና ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ዓምዶም ገብረ ሥላሴ፣ በቅርቡ በብዙኀን መገናኛዎች የሚስተዋለው በመግለጫዎች መካሰስ፣ “ሕዝብ እንዳይረጋጋ የሚያደርግ ነው፤” ብለዋል፡፡

የሣልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀ መንበር አቶ አሉላ ኀይሉ ደግሞ፣ የሰላም ስምምነቱን በሚጥስ መልኩ፣ በፌደራሉ መንግሥት ብዙኀን መገናኛ፣ በጦርነቱ ወቅት ይነገሩ የነበሩ የፕሮፓጋንዳ ይዘቶች እየተሰራጩ ናቸው፤ ሲሉ ከሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ/ኢዜማ/ የሕዝብ ግንኙንት ኃላፊ ዶክተር ሙሉዓለም ተናኘወርቅ በበኩላቸው፣ ኹሉም አካላት፣ የግጭት ጊዜ ተጎጂዎች ሰላማዊ ዜጎች መኾናቸውን ተገንዝበው ለሰላም በተግባር እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ከፌደራሉ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳክም፡፡ ከአሁን በፊት ህወሓት ባወጣው መግለጫ፣ ሰላም ስትራቴጂያዊ ምርጫው እንደኾነ ገልጿል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ደግሞ፣ መንግሥት፣ ለስምምነቱ ትግበራ እና ለትግራይ ሕዝብ ፍላጎት መሟላት እየተጋ ነው፤ ሲሉ፣ ባለፈው ሳምንት መግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG