በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በበቴ ዑርጌሳ ግድያ ላይ ሙሉ ምርመራ እንዲካሔድ ጥሪ አቀረበች


ዩናይትድ ስቴትስ በበቴ ዑርጌሳ ግድያ ላይ ሙሉ ምርመራ እንዲካሔድ ጥሪ አቀረበች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:28 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ፣ በኦነግ የፖሊቲካ ዘርፍ ኃላፊ በቴ ዑርጌሳ ግድያ ላይ ሙሉ ምርመራ እንዲካሔድ ጥሪ አቀረበች።

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥርያ ቤት የአፍሪቃ ጉዳዮች ቢሮ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው፣ ትላንት ረቡዕ እኩለ ሌሊት ላይ፣ በመቂ ከተማ የተፈጸመው የአቶ በቴ ዑርጌሳ ግድያ ተጣርቶ ተጠያቂዎች ለሕግ መቅረባቸው፣ በአገሪቱ ሁከት እንዳይቀጥል ይረዳል፤ ብሏል።

ግድያውን የኮነኑት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና ሌሎችም የፖሊቲካ ፓርቲዎች፣ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቀዋል። በሌላ በኩል፣ የአቶ በቴ ዑርጌሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት፣ ዛሬ ኀሙስ በመቂ ከተማ መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG