በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት እና አለመረጋጋት የሆቴሎችን የክፍሎች ኪራይ እና ገቢ በ50 ከመቶ ቀንሷል


ግጭት እና አለመረጋጋት የሆቴሎችን የክፍሎች ኪራይ እና ገቢ በ50 ከመቶ ቀንሷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:51 0:00

በኢትዮጵያ፣ የሆቴሎች ሥራ እቅንስቃሴ እየተዳከመ ነው፡፡ የሆቴሎች የመኝታ ክፍሎች ኪራይ ከ50 ከመቶ በታች መኾኑንና አንዳንዶቹም የባንክ ዕዳ መክፈል እየተሳናቸው በኪሳራ እየተዘጉ እንደሚገኙ፣ የሆቴል ባለሞያዎች እና የሥራ መሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ የሚገኝ የአንድ ባለአራት ኮከብ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ተስፋዬ እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም እና ሆቴል ገበያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ዓለሙ፣ ለሆቴሎቹ ሥራ መቀዛቀዝ፥ በአገሪቱ በሚታየው ግጭት እና አለመረጋጋት ሳቢያ፣ የቱሪዝም መዳከምና የውጭ ምንዛሪ ጉድለት አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በተለይ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ እና የአማራ ክልሎች እውቅ የቱሪስት መስሕቦች አካባቢ የሚገኙ ሆቴሎች፣ ዋናዎቹ ተጎጂዎች እንደኾኑ አስረድተዋል፡፡

ከአምስት ዓመት በተለይም ከኮሮና ወረርሽኝ በፊት፣ የሆቴሎች አማካይ ገቢ፣ ከመኝታ ክፍሎቻቸው 75 ከመቶዎቹን በማከራየት የሚገኝ እንደነበረ የሥራ መሪዎቹ አውስተዋል፡፡ ችግሩ የክፍሎቹ አለመያዝ ብቻ ሳይኾን፣ ክፍያውም በዶላር መኾኑ ቀርቶ በብር መፈጸሙ የገቢ ማሽቆልቆል ማስከተሉን አስረድተዋል፡፡

የሆቴሎች የጥራት ጉድለት፣ ደንበኞችንና ጎብኝዎችን የሚስቡ የማስታወቂያ ሥራዎችን አለመሥራትና ከኹኔታዎች ጋራ የተናበበ የዋጋ ለውጦችን አለማድረግ፣ በሆቴሎች በኩል የሚታይ ችግሮ ኾኖ ተጠቅሷል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይድ ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG