በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሐዲያ ዞን የታሰሩት የዳንጣ ማኅበረሰብ 14 ወጣቶች በዋስ ተፈቱ


በሐዲያ ዞን የታሰሩት የዳንጣ ማኅበረሰብ 14 ወጣቶች በዋስ ተፈቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:29 0:00

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሐዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ፣ የዳንጣ ልማት ማኅበር ምሥረታን ሲያስተባብሩ የነበሩ 14 ወጣቶች፣ በ20ሺሕ ዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉ፣ ትላንት ማክሰኞ የተሰየመው፣ የሐዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጠ። ከታሳሪዎቹ የአንዱ አባት አቶ ሞገስ ለፌቦ፣ ውሳኔውን ተከትሎ ልጃቸው ከእስር መፈታቱን ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።

ወጣቶቹ፣ በልማት ማኅበር ምሥረታ ላይ በመሳተፋቸው ብቻ መታሰራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት የአካባቢው ነዋሪ አቶ አበበ አዴሎ፣ ቀድሞውኑም የታሰሩት “ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ነበር፤” ብለዋል።

በዋስ ከተፈቱት ወጣቶች መካከል የኾነው ደምስ መሠረት ደግሞ፣ ወጣቶቹ የታሰሩት ያልተፈቀደ ሰልፍ በማድረግ ተጠርጥረው መኾኑን ገልጾ፣ ለሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. መቀጠራቸውን ነግሮናል።

ስለታሰሩት ወጣቶች የአሜሪካ ድምፅ ከሁለት ሳምንት በፊት የጠየቃቸው የሶሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ዴቶሬ፣ በወንጀል አድራጎት ተጠርጥረው እንደኾነ ገልጸው፣ የልማት ማኅበር ምሥረታ ውስጥ በመሳተፋቸውና የማንነት ጥያቄ በማንሣታቸው ነው፤ መባሉን ማስተባበላቸው ይታወቃል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG