በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአድማ ላይ የሚገኙት የኬንያ ሐኪሞች ሠልፍ አደረጉ


ፎቶ ፋይል፦ የኬንያ የህክምና ባለሞያዎች ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ እአአ መጋቢት 22/2024
ፎቶ ፋይል፦ የኬንያ የህክምና ባለሞያዎች ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ እአአ መጋቢት 22/2024

በኬንያ የሚገኙ የጤና ሠራተኞ የሚያደርጉት የሥራ ማቆም አድማ አራተኛ ሳምንቱ በተቃረበበት ወቅት፣ በመቶ የሚቆጠሩ ዶክተሮች ትናንት በመዲናዋ ናይሮቢ ሠልፍ አድርገዋል።

ሰባት ሺሕ ዓባላት ያሉት የጤና ሠራተኞች ማኅበር፣የተሻለ ክፍያ እና የሥራ ሁኔታ በመጠየቅ አድማ መቷል። በዚህም ምክንያት በሃገሪቱ በሚገኙ 57 ሆስፒታሎች ሥራው ተስተጓጉሏል።

“ወደ ሆስፒታል ሥራችን መመለስ ብንፈልግም፣ በመንግሥት በግዳጅ የምንመለስ ከሆነ፣ የሠውን ስቃይ የሚያስቆም አይሆንም” ሲሉ የማኅበሩ ምክትል ዋና ፀሃፊ ዴኒስ ሚስኬላ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

ሐኪሞቹ በፓርላማ በመገኘት ቅሬታቸውን በጽሑፍ አቅርበዋል።

ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ሥልጣን የመጡት ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ፣ ወጪ ቅነሳ ላይ ያተኮሩ ርምጃዎችን ሲወስዱ የቆዩ ሲሆን፣ ለሐኪሞቹ ተጨማሪ የሚሰጥ ነገር እንደሌለ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG