በሰሜን ምስራቅ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ታጣቂ ሚሊሻዎች በፈጸሙት ጥቃት 15 ሰዎችን መግደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት እና ነዋሪዎች አስታወቁ።
በምህጻሩ ኮዴኮ ተብሎ በሚታወቀው ‘የኮንጎ የልማት ትብብር’ በተሰኘው ታጣቂ ቡድን ምክንያት በዚህ በያዝነው በጎርጎሮሳዊያኑ ዓመት በወርቅ መዓድን ስፍራ የሚሰሩ ብዙዎች መገደላቸው ተገልጿል።
የቅርብ ጊዜው ጥቃት ጋሊ እና ኢቱሪ በተሰኙት አካባቢዎች ነው የተፈጸመው። ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ የግብረ ሰናይ ተቋም ባልደረባ ሰባት ሴቶችን ጨምሮ 16 ሟቾች በመንደሩ አደባባይ ላይ ተገድለው ማየታቸውን ተናግረዋል። አክሽን አጌንስት ሀንገር የተሰኘው የእርዳታ ቡድን በኮዴኮ ታጣቂዎች በሚደርሰው ጥቃት የተነሳ በኢቱሪ አውራጃ ድጋፍ ማድረግ ማቋረጡን አስታውቋል።
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለዓመታት ከዘለቀው ሰላም በኋላ በጎርጎርሳዊያኑ 2017 አንስቶ ግጭቶች እየጨመሩ መጥተዋል። የመንግስታቱ ድርጅት በግጭቶቹ የተነሳ በሺዎች ሲሞቱ 1.5 ሚሊየን ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም