በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፖሊስ በተበተነው የመቀሌ የተማሪዎች ሰልፍ ዐሥር ተሳታፊዎች ታስረዋል


በፖሊስ በተበተነው የመቀሌ የተማሪዎች ሰልፍ ዐሥር ተሳታፊዎች ታስረዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:43 0:00

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ያካሔዱት ሰልፍ በጸጥታ ኀይሎች ተበተነ። 10 ሰልፈኞችም እንደታሰሩ፣ ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በጦርነት ምክንያት መመረቅ ከሚገባቸው ጊዜ በሁለት ዓመት እንደዘገዩ የገለጹት ተማሪዎቹ፣ ዘንድሮም እንደማይመረቁ ዩኒቨርሲቲው በማሳወቁ፣ ውሳኔውን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸውን አመልክተዋል፡፡

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ ጉዳዩን አስመልክቶ ከትምህርት ሚንስትር ጋራ እየተነጋገረበት እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ ሰልፉን በኀይል የበተነው፣ የከተማው አስተዳደር የማያውቀው ስለኾነ ነው፤ ብሏል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG