በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን ለመተግበር ገለልተኛ ሥርዓት እንዲዘረጋ ተጠየቀ


የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን ለመተግበር ገለልተኛ ሥርዓት እንዲዘረጋ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:56 0:00

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት የኾኑ 43 ሀገራት፣ በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን ለመተግበር የሚያስችል ገለልተኛ ሥርዓት እንዲዘረጋ ጠይቀዋል፡፡

አገራቱ በጄኔቫ እየተካሔደ ለሚገኘው 55ኛው የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባቀረቡት የጋራ መግለጫ፣ “በኢትዮጵያ በጦርነት የተጎዱት ዜጎች ፍትሕ ይሻሉ፤” ሲሉ አመልክተዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ፣ በአገሪቱ ሊተገበር የታሰበው የሽግግር ፍትሕ ሒደት፥ ተኣማኒ፣ ነጻ እና ግልጽ እንዲኾን አገራቱ ጠይቀዋል፡፡

በመግለጫው ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዲሬክተር አቶ ያሬድ ኀይለ ማርያም፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ሊጸድቅ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ባለበት ኹኔታ፣ እንዲህ ዓይነት ዓለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቱ መልካም እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG