በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገር ቤት መሸኘቷን ገለጸች


ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገር ቤት መሸኘቷን ገለጸች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00

ኢትዮጵያ እና ፑንትላንድ፣ በአዲስ አበባ የሁለትዮሽ ውይይት ባደረጉ ማግስት፣ ሶማሊያ የአትዮጵያን አምባሳደር ከአገሯ ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን አስታውቃለች፡፡

በተጨማሪም፣ በሶማሊላንድ እና በፑንትላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶችን እንዲዘጉ ወስና ቀነ ገደብ ማስቀመጧን ይፋ አድርጋለች፡፡ “የቆንስላው ጉዳይ ሶማሊያን አይመለከታትም” ያሉት ሶማሊላንድ እና ፑንትላንድ በበኩላቸው፣ ውሳኔውን “ተራ ሕልም” ሲሉ አጣጥለዋል፡፡

የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ ጃማ፣ ለውሳኔው ምክንያቱ “ኢትዮጵያ በሶማሊያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን መቀጠሏ ነው፤” ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ የሰጠው ምላሽ አለመኖሩን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በፑንትላንድ መካከል ትላንት የተደረገው ውይይት፣ ከሰሞናዊ ጉዳዮች ጋራ ግንኙነት እንደሌለውም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የሚገኙ 70ሺሕ ዜጎችን በዘመቻ የመመለስ ሥራ በቅርቡ እንደምትጀምር ቃል አቀባዩ አያይዘው ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG